" ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ. 4፥5-6)
" Let your moderation( Gentleness) be known unto all men. THE LORD IS AT HAND. Be careful for nothing; but in every thing by prayer and supplication with thanksgiving let your requests be made known unto God."-
" እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ። ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 1፥14-17)
" as children of obedience, not conforming yourselves according to your former lusts as in your ignorance, but just as he who called you is holy, you yourselves also be holy in all of your behavior; because it is written, "You shall be holy; for I am holy." If you call on him as Father, who without respect of persons judges according to each man's work, pass the time of your living as foreigners here in reverent fear:"(1 Peter Chap. 1:14-17)-
" የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል..."(ትንቢተ ኢሳይያስ 30:15)
ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ!!!
"For thus said the Lord God(Yahweh), the Holy One of Israel, "You will be saved in returning and rest. Your strength will be in quietness and in confidence."..."(Isaiah 30:15) SEE THAT YOU DON'T REFUSE HIM WHO SPEAKS!!!-
"... በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤ ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ። " (የይሁዳ መልእክት ምዕ. 1፥1-2)
" --- to them that are sanctified by God the Father, and preserved in Jesus Christ, and called: MERCY unto you, and PEACE, and LOVE, BE MULTIPLIED. "(Jude Chap. 1:1-2)-
"There is neither Jew nor Greek, there is neither slave(bond) nor free man, there is neither male nor female; for you are all one in Christ Jesus."(Galatians 3:28)
-
" አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። " (ኦሪት ዘፍጥረት 4:10)
" And He (Yahweh) said, What have you done? The voice of your brother's blood cries to me from the ground." (Genesis 4:10)-
" ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ። "(መጽሐፈ መክብብ 9:12)
" ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። "(ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕ. 5፥16:17)
ሞኝ ምን እየሆነ እና ምን እየተደረገ እንዳለ ምን ዓይነት ዘመን ላይ እንዳለ አያውቅም። ሁልጊዜ ፋሲካ ይመስለዋል። ጠቢብ ግን ሁሉን እየመረመረ ያስባል፣ ያስተውላል፣ ይናገራል፣ ይራመዳል፣ ይኖራል...-
" የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5:20)
አንዳንዶቻችን ልናመልከው የሚገባንን እውነተኛውን አምላክ፣ ልንጓዝበት የሚገባንን እውነተኛውን መንገድ፣ ልንኖረው የሚገባንን እውነተኛው ሕይወት... ከሐሰተኛው በምን ለይተን ልናውቀው እንችላለን? ብለን ስንጠይቅ እንሰማለን። ነገር ግን መጽሓፍ ይህንን ለይተን ማወቅ የምንችልበትን ልብ ተሰጥቷችሃል እያለን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደመጣ የሰማ ሁሉ እውነተኛውን ከሐሰተኛው ለይቶ ለማወቅ የሚያስችለው ልብ ተሰጥቶታል። ስለዚህ እርሱ ብቻ እውነተኛ አምላክ ስለሆነ እርሱን በማምለክ ጸንተን በመቆም የዘላለምን ሕይወት እንኑር። ወደ ግራም ወደ ቀኝም መገላመጥ አያስፈልግም!!!
-
" ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
" (የማቴዎስ ወንጌል 6:34)
ስንቶቻችን ነን ይህንን ቃል እያወቅን ነገር ግን በተግባር ቃሉ እንደሚለን መሆን እና መኖር ያቃተን። አንድ ነገር ማወቅ ያለብን ግን በራሳችን እንደ ቃሉ መኖርም ሆነ መሆን የማንችል መሆናችንን ነው። ጌታ እራሱ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም፤ ደግሞም ለደቀ-መዛሙርቱ ኃይልን ከዓርያም( ከላይ) እስክትለብሱ ከኢየሩሳሌም አትውጡ ነበር ያላቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ማለቱን ልብ ልንል ይገባናል!!!-
"የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው፤ ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና። "(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 1፥7-9)
እግዚአብሔርን መፍራት ማለት በእርሱ ላይ መደገፍ፣ በእርሱ መመካት፣ በእርሱ መታመን፣ አድርግ አታድርግ የሚለኝ ሁሉ ለእኔ ጥቅም ሲል ነው ብሎ ሳይጠራጠሩ ማመን ማለት ነው። ይህንን አውቆ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበበኛ እና አስተዋይ፤ ከመከራ ሥጋትም አርፈን በእርጋታ እንድንቀመጥ፤ ክብር እና ውበት እንድንቀዳጅ... ያደርጋል!!! እንዲህ አድርገን ሳናውቅ ወይም ሳንረዳ እግዚአብሔርን መፍራት ደግሞ አላዋቂ፣ ሰነፍ፣ ቸልተኛ፣ ፌዘኛ እና ኃጢያተኛ እንድንሆን ያደርገናል!!!-